ዘፍጥረት 46:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባ ለልጁ ለልያ የሰጣት የዘለፋ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ እርስዋም እነዚህን ዐሥራ ስድስቱን ነፍስ ለያዕቆብ ወለደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ዐሥራ ስድስት ልጆች ሁሉ፣ ላባ ለልጁ ለልያ ከሰጣት ከዘለፋ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ዐሥራ ስድስቱ ላባ ለልጁ ለልያ በሞግዚትነት ከሰጣት ከዚልፋ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ዐሥራ ስድስቱ ላባ ለልጁ ለልያ በሞግዚትነት ከሰጣት ከዚልፋ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባ ለልጁ ለልያ የሰጣት የዘለፋ ልጆች እነዚህ ናቸው እነዚህን አሥራ ስድስቱንም ነፍስ ለያዕቆብ ወለደች። |
የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆችም፤ ጋድ፥ አሴር፤ እነዚህ በሁለቱ ወንዞች መካከል በሶርያ የተወለዱለት የያዕቆብ ልጆች ናቸው።