La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 45:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮሴ​ፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታ​ገሥ አል​ተ​ቻ​ለ​ውም፥ “ሰዎ​ቹ​ንም ሁሉ ከፊቴ አስ​ወ​ጡ​ልኝ” ብሎ ተና​ገረ፤ ዮሴፍ ለወ​ን​ድ​ሞቹ ራሱን በገ​ለጠ ጊዜ በእ​ርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ጊዜ ዮሴፍ አጠገቡ በነበሩ ሰዎች ፊት ስሜቱን ሊገታ ባለመቻሉ፣ “እዚህ ያሉትን ሰዎች በሙሉ አስወጡልኝ” ብሎ ጮኾ ተናገረ፤ ስለዚህም ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ በገለጠበት ጊዜ፣ ከርሱ ጋራ ሌላ ማንም ሰው አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮሴፍም በእርሱ ዘንድ ቆመው ባሉት ሰዎች ሁሉ ፊት ሊታገሥ አልተቻለውም፦ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ጮኾ ተናገረ፥ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ ማንም ከአጠገቡ የቆመ አልነበረም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮሴፍ የናፍቆት ስሜቱን በአገልጋዮቹ ፊት መቈጣጠር ባለመቻሉ “ሁላችሁም ከዚህ ውጡ” ብሎ አዘዘ፤ ስለዚህ ዮሴፍ ማንነቱን ለወንድሞቹ በገለጠ ጊዜ ማንም የውጪ ሰው በአጠገቡ አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮሴፍም በእርሱ ዘንድ ቆመው ባሉት ሰዎች ሁሉ ፊት ሊታገሥ አልተቻለውም፦ ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ ብሎ ጮኽ ተናገረ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 45:1
12 Referencias Cruzadas  

ዮሴ​ፍም ከእ​ነ​ርሱ ዘወር ብሎ አለ​ቀሰ፤ ደግ​ሞም ወደ እነ​ርሱ ተመ​ልሶ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ስም​ዖ​ን​ንም ከእ​ነ​ርሱ ለይቶ ወስዶ በፊ​ታ​ቸው አሰ​ረው።


አለ​ዚ​ያም ብላ​ቴ​ናው ከእኛ ጋር ከሌለ እኔ ወደ አባ​ታ​ችን እን​ዴት እሄ​ዳ​ለሁ? አባ​ታ​ች​ንን የሚ​ያ​ገ​ኘ​ውን መከራ እን​ዳ​ላይ።”


የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሴቶች ልጆች ደስ እን​ዳ​ይ​ላ​ቸው፥ የቈ​ላ​ፋ​ንም ሴቶች ልጆች እልል እን​ዳ​ይሉ፥ በጌት ውስጥ አታ​ውሩ፤ በአ​ስ​ቀ​ሎ​ናም አደ​ባ​ባይ የም​ስ​ራች አት​በሉ።


ምጣ​ዱ​ንም ወስዳ በፊቱ ገለ​በ​ጠች፤ እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አም​ኖ​ንም፥ “ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስ​ወጡ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ ወጣ።


ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዝም እላ​ለ​ሁን? አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እታ​ገ​ሣ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ለሁ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም እጨ​ር​ሳ​ለሁ።


እኔም እን​ዲህ አልሁ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አላ​ነ​ሣም፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በስሙ አል​ና​ገ​ርም፥” በአ​ጥ​ን​ቶች ውስጥ እንደ ገባ እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነ​ብኝ፤ ደከ​ምሁ፤ መሸ​ከ​ምም አል​ቻ​ል​ሁም።


በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


“ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤


ይኸ​ውም ለሕ​ዝቡ ሁሉ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን አስ​ቀ​ድሞ ለመ​ረ​ጣ​ቸ​ውና ምስ​ክ​ሮች ለሚ​ሆ​ኑት ብቻ ነው እንጂ፤ የመ​ረ​ጣ​ቸው የተ​ባ​ል​ንም እኛ ነን፤ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ ከተ​ነሣ በኋላ ከእ​ርሱ ጋር የበ​ላን የጠ​ጣ​ንም እኛ ነን።


ወደ ግብ​ፅም እንደ ገና በተ​መ​ለሱ ጊዜ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ዐወ​ቁት፤ ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ዘመ​ዶች ዐወ​ቃ​ቸው።


ብቻ​ዬን ይድ​ላኝ አያ​ሰ​ኝም፤ አያ​በ​ሳ​ጭም፤ ክፉ ነገ​ር​ንም አያ​ሳ​ስ​ብም።