ዘፍጥረት 44:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋይህ አባታችንም እንዲህ አለን፦ ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆችን እንደ ወለደችልኝ እናንተ ታውቃላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አገልጋይህ አባቴም እንዲህ አለን፤ ‘ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆች እንደ ወለደችልኝ ታውቃላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋይህ አባቴም እንዲህ አለን፤ ‘ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆች እንደ ወለደችልኝ ታውቃላችሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባታችንም እንዲህ አለን፤ ‘ሚስቴ ራሔል ሁለት ወንዶች ልጆች ብቻ እንደ ወለደችልኝ ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆችን እንደ ወለደችልኝ እናንተ ታውቃላችሁ፤ |
እርሱም አለ፥ “ልጄ ከእናንተ ጋር አይወርድም፤ ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና፤ በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፉ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።”
እኛም አልነው፦ ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ካልሄደ መሄድ አንችልም፤ ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ከሌለ የዚያን ሰው ፊት ማየት አይቻለንምና።