ዘፍጥረት 44:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛም አልነው፦ ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ካልሄደ መሄድ አንችልም፤ ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ከሌለ የዚያን ሰው ፊት ማየት አይቻለንምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘መሄድ አንችልም፤ መሄድ የምንችለው ታናሽ ወንድማችን ዐብሮን ሲሄድ ብቻ ነው። ታናሽ ወንድማችንን ይዘን ካልሄድን በቀር፣ የሰውየውን ፊት ማየት አንችልም’ አልነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘መሄድ አንችልም፤ መሄድ የምንችለው ታናሽ ወንድማችን አብሮን ሲሄድ ብቻ ነው። ታናሽ ወንድማችንን ይዘን ካልሄድን በስተቀር፥ የሰውየውን ፊት ማየት አንችልም’ አልነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛም ‘ታናሽ ወንድማችን ከእኛ ጋር ካልሆነ በሰውየው ፊት መቅረብ አንችልም፤ ስለዚህ ወደዚያ መሄድ የምንችለው ታናሽ ወንድማችን ከእኛ ጋር የሄደ እንደሆን ብቻ ነው’ አልነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛም አልነው፦ እንሄድ ዘንድ አይሆንልንም ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ይወርድ እንደ ሆነ እኝም እንወርዳለን ታናሹ ወንድማችን ከእኝ ጋር ከሌለ የዚያን ሰው ፊት ማየት አይቻለንምና ባሪያን አባቴም እንዲህ አለን፦ |
ያ ወዳጁም ከውስጥ ሆኖ፦ ‘አትዘብዝበኝ፤ ደጁን አጥብቀን ዘግተናል፤ ልጆችም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል፤ እሰጥህ ዘንድ መነሣት አልችልም’ ይለዋልን?