ይሁዳም እንዲህ አለው፥ “የሀገሩ ጌታ ያ ሰው፦ ‘ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ከአልመጣ ፊቴን አታዩም’ ብሎ በምስክር ፊት አዳኝቶብናል።
ዘፍጥረት 44:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ጌታችንም አገልጋዮችህን፦ ታናሽ ወንድማችሁን ከእናንተ ጋር ከአላመጣችሁት ዳግመኛ ፊቴን አታዩም አልኸን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ግን እኛን አገልጋዮችህን፣ ‘ታናሽ ወንድማችሁ ዐብሯችሁ ወደዚህ ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ አልኸን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን እኛን አገልጋዮችህን፥ ‘ታናሽ ወንድማችሁ አብሮአችሁ ወደዚህ ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ አልኸን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታችንም ለአንተ ለጌታችን ነግረንህ አገልጋዮቹን ‘ታናሽ ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ በፊቴ አትቀርቡም’ ብለህ በብርቱ አስጠነቀቅከን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባርያዎችህንም፦ ታናሽ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን አታዮም አልኽን። |
ይሁዳም እንዲህ አለው፥ “የሀገሩ ጌታ ያ ሰው፦ ‘ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ከአልመጣ ፊቴን አታዩም’ ብሎ በምስክር ፊት አዳኝቶብናል።
ወንድማችንን ከእኛ ጋር ባትልከው ግን አንሄድም፤ ያ ሰው ‘ታናሽ ወንድማችሁን ከእናንተ ጋር ካላመጣችሁ ፊቴን አታዩም’ ብሎናልና።”