ዮሴፍም ዐይኑን አንሥቶ የእናቱን ልጅ ወንድሙ ብንያምን አየው፤ እርሱም አለ፥ “ወደ አንተ እናመጣዋለን ብላችሁ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነውን?” እነርሱም፥ “አዎን” አሉት። እንዲህም አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ።”
ዘፍጥረት 44:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታዬ አገልጋዮችህን፦ አባት አላችሁን? ወይስ ወንድም? ብለህ ጠየቅሃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታዬ፣ ‘አባት ወይም ወንድም አላችሁ?’ ብሎ አገልጋዮቹን ጠይቆ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታዬ ‘አባት ወይም ወንድም አላችሁ?’ ብሎ አገልጋዮቹን ጠይቈ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታዬ ከአሁን ቀደም ‘አባት አላችሁ ወይ? ሌላ ወንድምስ አላችሁ ወይ?’ ብለህ ጠየቅከን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታዬ ባሪያዎቹን፦ አባት አላችሁን ወይስ ወንድም? ብሎ ጠየቀ። |
ዮሴፍም ዐይኑን አንሥቶ የእናቱን ልጅ ወንድሙ ብንያምን አየው፤ እርሱም አለ፥ “ወደ አንተ እናመጣዋለን ብላችሁ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነውን?” እነርሱም፥ “አዎን” አሉት። እንዲህም አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ።”
እነርሱም አሉ፥ “ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ትውልዳችን ፈጽሞ ጠየቀን፤ እንዲህም አለን፦ ‘ሽማግሌው አባታችሁ ገና በሕይወት ነው? ወንድምስ አላችሁን?’ እኛም እንደዚሁ እንደ ጠየቀን መለስንለት፤ በውኑ፦ ‘ወንድማችሁን አምጡ’ እንዲለን እናውቅ ነበርን?”
እኛም ለጌታዬ እንዲህ አልን፦ ሽማግሌ አባት አለን፤ በሽምግልናው የወለደውም ታናሽ ብላቴና አለ፤ ወንድሙ ግን ሞተ፤ ለእናቱም እርሱ ብቻውን ቀረ፤ አባቱም ይወድደዋል።