ከእነርሱም አንዱ በአደሩበት ስፍራ ለአህዮቹ ገፈራን ይሰጥ ዘንድ ዓይበቱን ፈታ፤ ብሩንም በዓይበቱ አፍ ተቋጥሮ አገኘ።
ዘፍጥረት 44:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እየራሳቸውም ፈጥነው ዓይበታቸውን ወደ ምድር አወረዱ፤ እየራሳቸውም ዓይበታቸውን ፈቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱ ሰው ጭነቱን ወዲያውኑ አራግፎ ስልቻውን ፈታ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እያንዳንዱ ሰው ጭነቱን ወዲያውኑ አራግፎ ስልቻውን ፈታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በፍጥነት ስልቻዎቻቸውን አወረዱ፤ እያንዳንዱም የራሱን ስልቻ ከፈተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እየራሳቸውም ፈጥነው ዓይበታቸውን ወደ ምድር አወረዱ፥ እየራሳቸውም ዓይበታቸውን ፈቱ። |
ከእነርሱም አንዱ በአደሩበት ስፍራ ለአህዮቹ ገፈራን ይሰጥ ዘንድ ዓይበቱን ፈታ፤ ብሩንም በዓይበቱ አፍ ተቋጥሮ አገኘ።
እርሱም አለ፥ “አሁንም እንዲሁ እንደ ነገራችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ አገልጋይ ይሁነኝ፤ እናንተም ንጹሓን ትሆናላችሁ።”