ወንድማችንን ከእኛ ጋር ባትልከው ግን አንሄድም፤ ያ ሰው ‘ታናሽ ወንድማችሁን ከእናንተ ጋር ካላመጣችሁ ፊቴን አታዩም’ ብሎናልና።”
ዘፍጥረት 43:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም አላቸው፥ “በእኔ ላይ ያደረጋችኋት ይህች ክፋት ምንድን ናት? በዚያውስ ላይ ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለምን ነገራችሁት?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልም፣ “ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለዚያ ሰው በመንገር ለምን ይህን ችግር እንዲደርስብኝ አደረጋችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም፥ “ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለዚያ ሰው በመንገር ለምን ይህን ችግር እንዲደርስብኝ አደረጋችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም “ ‘ሌላ ወንድም አለን’ ብላችሁ ለሰውየው በመናገር ለምን ይህን ያህል መከራ አመጣችሁብኝ?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም አላቸው ለምን በደላችሁኝ? ለዚያውስ፦ ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለምን ነገራችሁን? |
ወንድማችንን ከእኛ ጋር ባትልከው ግን አንሄድም፤ ያ ሰው ‘ታናሽ ወንድማችሁን ከእናንተ ጋር ካላመጣችሁ ፊቴን አታዩም’ ብሎናልና።”
እነርሱም አሉ፥ “ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ትውልዳችን ፈጽሞ ጠየቀን፤ እንዲህም አለን፦ ‘ሽማግሌው አባታችሁ ገና በሕይወት ነው? ወንድምስ አላችሁን?’ እኛም እንደዚሁ እንደ ጠየቀን መለስንለት፤ በውኑ፦ ‘ወንድማችሁን አምጡ’ እንዲለን እናውቅ ነበርን?”
ሙሴንም አሉት፥ “በግብፅ መቃብር ስላልኖረ በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ አወጣኸን? ከግብፅ ታወጣን ዘንድ ይህ ያደረግህብን ምንድን ነው?