ዘፍጥረት 43:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድማችንን ከእኛ ጋር ባትልከው ግን አንሄድም፤ ያ ሰው ‘ታናሽ ወንድማችሁን ከእናንተ ጋር ካላመጣችሁ ፊቴን አታዩም’ ብሎናልና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱን የማትልከው ከሆነ ግን እኛም ወደዚያ አንወርድም፤ ያም ሰው፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱን የማትልከው ከሆነ ግን እኛም ወደዚያ አንወርድም፤ ያም ሰው፥ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን የማትፈቅድልን ከሆነ ግን ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ እፊቴ እንዳትቀርቡ’ ስላለን ወደዚያ አንሄድም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያ ሰው፦ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዮም ብሎናልና። |
ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡ፤ ነገራችሁ የታመነ ይሆናልና፤ ይህ ከአልሆነ ግን ትሞታላችሁ።” እንዲህም አደረጉ።
እርሱም አለ፥ “ልጄ ከእናንተ ጋር አይወርድም፤ ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና፤ በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፉ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።”
ይሁዳም እንዲህ አለው፥ “የሀገሩ ጌታ ያ ሰው፦ ‘ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ከአልመጣ ፊቴን አታዩም’ ብሎ በምስክር ፊት አዳኝቶብናል።
እስራኤልም አላቸው፥ “በእኔ ላይ ያደረጋችኋት ይህች ክፋት ምንድን ናት? በዚያውስ ላይ ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለምን ነገራችሁት?”
አንተ ጌታችንም አገልጋዮችህን፦ ታናሽ ወንድማችሁን ከእናንተ ጋር ከአላመጣችሁት ዳግመኛ ፊቴን አታዩም አልኸን።
እኛም አልነው፦ ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ካልሄደ መሄድ አንችልም፤ ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ከሌለ የዚያን ሰው ፊት ማየት አይቻለንምና።
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።