ዮሴፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታገሥ አልተቻለውም፥ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ተናገረ፤ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም።
ዘፍጥረት 43:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊቱንም ታጥቦ ተጽናንቶም ወጣ። “እንጀራ አቅርቡልን” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊቱን ከታጠበ በኋላ ተመልሶ፣ ስሜቱን በመቈጣጠር፣ “ማእድ ይቅረብ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊቱን ከታጠበ በኋላ፥ ተመልሶ፥ ስሜቱን በመቈጣጠር፥ “ማእድ ይቅረብ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፊቱንም ከታጠበ በኋላ ወጣ፤ ራሱንም በመቈጣጠር ምሳ እንዲቀርብ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊቱንም ታጥቦ ወጣ ልቡንም አስታግሦ፦ እንጀራ አቅርቡ አለ። |
ዮሴፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታገሥ አልተቻለውም፥ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ተናገረ፤ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም።
ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፤ እንግዲህ ለዘለዓለም ዝም እላለሁን? አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እታገሣለሁ፤ አጠፋለሁ፤ በአንድነትም እጨርሳለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ድምፅሽን ከልቅሶ፥ ዐይኖችሽንም ከእንባ ከልክዪ፤ ለሥራሽ ዋጋ ይሆናልና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከጠላትም ምድር ይመለሳሉ።