አባታቸው እስራኤልም እንዲህ አላቸው፥ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ ፤ ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ፤ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።
ዘፍጥረት 43:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም በእኩለ ቀን እስኪገባ ድረስ እነርሱ እጅ መንሻቸውን አዘጋጁ፤ ከዚያ ምሳ እንደሚበሉ ሰምተዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሳ በዚያ እንደሚበሉ ተነግሯቸው ስለ ነበር፣ ዮሴፍ በቀትር ከመግባቱ በፊት እጅ መንሻዎቻቸውን ለማበርከት ተዘጋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምሳ በዚያ እንደሚበሉ ተነግሯቸው ስለ ነበር፥ ዮሴፍ በቀትር ከመግባቱ በፊት እጅ መንሻዎቻቸውን ለማበርከት ተዘጋጁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዮሴፍ ጋር ምሳ እንደሚበሉ ተነግሮአቸው ስለ ነበር፥ ዮሴፍ በምሳ ሰዓት እስከሚመጣ ድረስ ለእርሱ የሚያቀርቡለትን ስጦታ አዘጋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም በእኩለ ቀን እስኪገባ ድረስ እነርሱ እጅ መንሻቸው አዘጋጁ ከዚያ እንጀራን እንደሚበሉ ሰምተዋልና። |
አባታቸው እስራኤልም እንዲህ አላቸው፥ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ ፤ ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ፤ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።
ሰዎቹም በእጃቸው ያችን እጅ መንሻና ብራቸውን በእጥፍ፥ ብንያምንም ከእነርሱ ጋር ወሰዱ፤ ተነሥተውም ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዮሴፍም ፊት ቆሙ፤ ሰገዱለትም።
ዮሴፍም ብንያምን ከእነርሱ ጋር በአየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “እነዚያን ሰዎች ወደ ቤት አስገባቸው፤ እርድም እረድ፤ አዘጋጅም፤ እነዚያ ሰዎች በእኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበላሉና።”