አብራምም፥ “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምን ትሰጠኛለህ? እነሆ፥ ልጅ ሳልወልድ እሞታለሁ፤ የቤቴም ወራሽ ከዘመዴ ወገን የሚሆን የደማስቆ ሰው የማሴቅ ልጅ ይህ ኢያውብር ነው” አለ።
ዘፍጥረት 43:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥም ቀረቡ፤ በቤቱም ደጅ ተናገሩት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ ቀርበው፣ በቤቱ መግቢያ ላይ አነጋገሩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ ቀርበው፥ በቤቱ መግቢያ ላይ አነጋገሩት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወደ ቤቱ በር አጠገብ ሲደርሱ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ፥ ቀረቡ በቤቱ ደጅ ተናገሩት እንዲህም አሉት፦ |
አብራምም፥ “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምን ትሰጠኛለህ? እነሆ፥ ልጅ ሳልወልድ እሞታለሁ፤ የቤቴም ወራሽ ከዘመዴ ወገን የሚሆን የደማስቆ ሰው የማሴቅ ልጅ ይህ ኢያውብር ነው” አለ።
ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡ፤ ነገራችሁ የታመነ ይሆናልና፤ ይህ ከአልሆነ ግን ትሞታላችሁ።” እንዲህም አደረጉ።
ዮሴፍም ብንያምን ከእነርሱ ጋር በአየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “እነዚያን ሰዎች ወደ ቤት አስገባቸው፤ እርድም እረድ፤ አዘጋጅም፤ እነዚያ ሰዎች በእኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበላሉና።”
እነዚያም ሰዎች ወደ ዮሴፍ ቤት እንደ ገቡ በአዩ ጊዜ እንዲህ አሉ፥ “በዓይበታችን ቀድሞ ስለ ተመለሰው ብር ሊተነኰሉብን፥ ሊወድቁብንም፥ እኛንም በባርነት ሊገዙን፥ አህዮቻችንንም ሊወስዱ ወደዚህ አስገቡን።”
ዮሴፍም የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “የእነዚህ ሰዎች ዓይበቶቻቸው መያዝ የሚችሉትን ያህል እህል ሙላላቸው፤ የሁሉንም ብር በየዓይበታቸው አፍ ጨምረው፤
ጌታችን ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፥ “መጋቢ የነበረው አንድ ባለጸጋ ሰው ነበረ፤ ገንዘቡን ሁሉ እንደሚበትን አድርገው በእርሱ ዘንድ ከሰሱት።