አሕዛብ ይገዙልህ፤ አለቆችም ይስገዱልህ፤ ለወንድምህ ጌታ ሁን፤ የአባትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
ዘፍጥረት 42:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም አሉት፥ “ጌታ ሆይ፥ አይደለም፤ ባሪያዎችህስ ስንዴ ሊገዙ መጥተዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን ሆይ፤ እንዲህስ አይደለም፤ አገልጋዮችህ የመጣነው እህል ለመሸመት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን ሆይ፤ እንዲህስ አይደለም፤ አገልጋዮችህ የመጣነው እህል ለመሸመት ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “ጌታችን ሆይ፥ እኛ ሰላዮች አይደለንም፤ እኛ አገልጋዮችህ እዚህ የመጣነው እህል ለመግዛት ነው” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም አሉት፦ ጌታችን ሆይ አይደለም ባሪያዎችህ ስንዴን ሊገዙ መጥተዋል፤ |
አሕዛብ ይገዙልህ፤ አለቆችም ይስገዱልህ፤ ለወንድምህ ጌታ ሁን፤ የአባትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው፥ “እነሆ ጌታህ አደረግሁት፤ ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች አደረግኋቸው፤ እህሉን፥ ወይኑንና ዘይቱንም አበዛሁለት፤ ለአንተ ግን፥ ልጄ ሆይ፥ ምን ላድርግልህ?”
ወንድሞቹም፥ “በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ገዢ ትሆነን ይሆን?” አሉት። እንደገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ የበለጠ ጠሉት።
አብድዩም በመንገድ ብቻውን ሳለ እነሆ፥ ኤልያስ ሊገናኘው ብቻውን መጣ፤ አብድዩም ሮጠና፥ በግንባሩ ወድቆ ሰገደለት፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ኤልያስ አንተ ነህን?” አለው።
ሳኦልም የዳዊት ድምፅ እንደ ሆነ ዐውቆ፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድምፅህ ነውን?” አለው። ዳዊትም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! አዎ እኔ ባሪያህ ነኝ” አለው።