ፈርዖን ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ፤ በዮሴፍም እጅ አደረገው፤ የነጭ ሐር ልብስንም አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ዝርግፍን አደረገለት፤
ዘፍጥረት 41:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው፤ ስገዱ እያለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እንዲሄድ አደረገ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማዕርግ ከርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ፣ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፣ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማዕረግ ከእርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ፥ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፥ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንጉሡ ሁለተኛ ሠረገላ ላይ እንዲቀመጥ አደረገው፤ የንጉሡም የክብር ዘብ ከፊት ፊት እየሄደ “እጅ ንሡ! እጅ ንሡ!” ይል ነበር፤ ዮሴፍ በግብጽ ምድር ላይ አስተዳዳሪ ሆኖ የተሾመው በዚህ ዐይነት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው አዋጅ ነጋሪም፦ ስገዱ እያለ በፊት በፊት ይጮኽ ነበር እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ተሾመ። |
ፈርዖን ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ፤ በዮሴፍም እጅ አደረገው፤ የነጭ ሐር ልብስንም አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ዝርግፍን አደረገለት፤
“የሀገሩ ጌታ የሆነው ሰው በክፉ ንግግር ተናገረን፤ የምድሪቱም ሰላዮች እንደሆን አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባን።”
የሀገሩም ጌታ ያ ሰው እንዲህ አለን፦ ‘ሰላማውያን ሰዎች ከሆናችሁ በዚህ ዐውቃለሁ፤ አንደኛውን ወንድማችሁን ከእኔ ጋር ተዉት፤ ለቤታችሁም የሸመታችሁትን እህል ይዛችሁ ሂዱ፤
ዮሴፍም በግብፅ ምድር ላይ ገዥ ነበረ፤ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ እህል ይሸጥ ነበር፤ የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግንባራቸው ሰገዱለት።
እንዲህም ብለው ነገሩት፥ “ልጅህ ዮሴፍ በሕይወቱ ነው፤ እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፤ አላመናቸውምም፤
አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ፤ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ፤ በቤቱም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግብፅ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ።
ከመከራውም ሁሉ አዳነው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።