ዘፍጥረት 41:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፥ “እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ገልጦልሃልና ከአንተ ይልቅ ብልህና ዐዋቂ ሰው የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለ ገለጠልህ፣ እንደ አንተ ያለ አስተዋይና ብልኅ ሰው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለ ገለጠልህ፥ እንዳንተ ያለ አስተዋይና ብልኅ ሰው የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ንጉሡ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሁሉ የገለጠልህ እግዚአብሔር ነው፤ ከማንኛውም ሰው ይልቅ አስተዋይና ብልኅ መሆንህ የተረጋገጠ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ እንደ አንተ ያለ ብልህ አዋቂም ሰው የለም እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ገልጦልሃልና። |
አንተም ዕዝራ፥ በእጅህ እንዳለው እንደ አምላክህ ጥበብ መጠን በወንዝ ማዶ ባሉ ሕዝብ ሁሉ፥ የአምላክህን ሕግ በሚያውቁ ሁሉ ላይ ይፈርዱ ዘንድ ጻፎችንና ፈራጆችን ሹም፤ የማያውቁትንም አስተምሩአቸው።
የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ይሆናሉ፤ ነገሥታትን የሚመክሩ ጥበበኞችም ምክራቸው ስንፍና ትሆናለች። ንጉሥን፥ “እኛ የጥበበኞች ልጆች፥ የቀደሙ ነገሥታትም ልጆች ነን እንዴት ትሉታላችሁ?”