ዘፍጥረት 41:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ሎሌዎቹን እንዲህ አላቸው፥ “በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰውን እናገኛለን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ማንን ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም፥ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ማንን ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረበት ከዮሴፍ የተሻለ ሰው ከቶ አናገኝም” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ሎሌዎቹን እንዲህ አላቸው፦ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰው እናገኛለንን? |
አንተም ዕዝራ፥ በእጅህ እንዳለው እንደ አምላክህ ጥበብ መጠን በወንዝ ማዶ ባሉ ሕዝብ ሁሉ፥ የአምላክህን ሕግ በሚያውቁ ሁሉ ላይ ይፈርዱ ዘንድ ጻፎችንና ፈራጆችን ሹም፤ የማያውቁትንም አስተምሩአቸው።
የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ይሆናሉ፤ ነገሥታትን የሚመክሩ ጥበበኞችም ምክራቸው ስንፍና ትሆናለች። ንጉሥን፥ “እኛ የጥበበኞች ልጆች፥ የቀደሙ ነገሥታትም ልጆች ነን እንዴት ትሉታላችሁ?”