ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈርዖን ጃንደረባ የመጋቢዎቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ወደ ግብፅ ከአወረዱት ከይስማኤላውያን እጅ ገዛው።
ዘፍጥረት 40:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስር ቤት ውስጥም ዮሴፍ ታስሮ በነበረበት የግዞት ስፍራ አጋዛቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው ዮሴፍ ወደ ተጋዘበትም እስር ቤት አስገባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው ዮሴፍ ወደ ተጋዘበትም እስር ቤት አስገባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ዮሴፍ ታስሮ ወደሚገኝበት ወደ ዘበኞች አለቃ ቤት ተወስደው እንዲታሰሩ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍ ታሰሮ በነበረበትም በግዛት ስፍራ በዘበኞቹ አለቃ ቤት አስጠበቃቸው። |
ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈርዖን ጃንደረባ የመጋቢዎቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ወደ ግብፅ ከአወረዱት ከይስማኤላውያን እጅ ገዛው።
የግዞት ቤቱም አለቃ በግዞት ያሉትን እስረኞች ሁሉ በዮሴፍ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዚያም የሚደረገው ነገር ሁሉ እርሱ የሚያደርገው ነበረ።
የግዞት ቤቱ ጠባቂዎች አለቃም በግዞት ቤት የሚደረገውን ሁሉ ምንም አያውቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮሴፍ ትቶለት ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረና፤ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ ያቀናለት ነበር።
የእስር ቤቱ ዘበኞች አለቃም ለዮሴፍ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ያገለግላቸው ነበር፤ በግዞት ቤትም አንድ ዓመት ተቀመጡ።