የእንጀራ አበዛዎቹ አለቃም ሕልሙን በመልካም እንደ ተረጐመለት በአየ ጊዜ ዮሴፍን እንዲህ አለው፥ “እኔም ደግሞ ሕልም አይች ነበር፤ እነሆም፥ ሦስት መሶብ ነጭ እንጀራ በራሴ ላይ ነበረ፤
ዘፍጥረት 40:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላይኛውም መሶብ ፈርዖን የሚበላው ጋጋሪው በያይነቱ የሠራው መብል ነበረበት፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከመሶቡ ይበሉ ነበር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በላይኛው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ የተለያየ ምግብ ነበረበት፤ ወፎችም ራሴ ላይ ካለው መሶብ ይበሉ ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በላይኛው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ የተለያየ ምግብ ነበረበት፤ ወፎችም ራሴ ላይ ካለው መሶብ ይበሉ ነበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሁሉ በላይ ባለው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ ልዩ ልዩ ምግብ ነበረበት፤ ነገር ግን ወፎች ምግቡን ከመሶቡ እያነሡ ይበሉት ነበር።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላይኛውም መሶብ ፈርዖን ከሚበላው ከጋጋዎች ሥራ ሁሉ ነበረበት፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከመሶቡ ይበሉ ነበር። |
የእንጀራ አበዛዎቹ አለቃም ሕልሙን በመልካም እንደ ተረጐመለት በአየ ጊዜ ዮሴፍን እንዲህ አለው፥ “እኔም ደግሞ ሕልም አይች ነበር፤ እነሆም፥ ሦስት መሶብ ነጭ እንጀራ በራሴ ላይ ነበረ፤
ዳዊትም ወደ ሴቄላቅ ሲሄድ ከምናሴ ወገን የምናሴ ሻለቆች የነበሩ ዓድና፥ ዮዛባት፥ ይዲኤል፥ ሚካኤል፥ ዮዛባት፥ ኤሊሁና ጼልታይ ወደ እርሱ ከዱ።