እንዲህም ሆነ፤ ፀሐይም በገባ ጊዜ ነበልባል መጣ፤ የእሳት መብራትና የሚጤስ ምድጃም መጣ፤ በዚያም በተከፈለው መካከል አለፈ።
ዘፍጥረት 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤልም ደግሞ ከበጎቹ መጀመሪያ የተወለደውንና ከሰቡት አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤልም መጀመሪያ ከተወለዱት በጎቹ መካከል ስባቸውን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። እግዚአብሔር ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም አቤል ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ። ጌታም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤልም ከበጎቹ መንጋ በመጀመሪያ የተወለደውን አንድ ጠቦት አመጣ፤ ካረደውም በኋላ የሰባውንና መልካም የሆነውን ብልት ሁሉ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እግዚአብሔርም በአቤልና በመሥዋዕቱ ደስ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም። |
እንዲህም ሆነ፤ ፀሐይም በገባ ጊዜ ነበልባል መጣ፤ የእሳት መብራትና የሚጤስ ምድጃም መጣ፤ በዚያም በተከፈለው መካከል አለፈ።
እናንተም የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈጣሪዬን የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ፤ ሰምቶም በእሳት የሚመልስ አምላክ፥ እርሱ አምላክ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መልካም ነው” ብለው መለሱ።
እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወረደች፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ እንጨቱንም፥ ድንጋዮቹንም በላች፤ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውኃ፥ አፈሩንም ላሰች።
ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱንም መሥዋዕት አቀረበ፤ እግዚአብሔርንም ጠራ፤ ከሰማይም ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት፤ እሳቱም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በላ።
ሰሎሞንም ይህን ጸሎት በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን ቍርባንና መሥዋዕቱን ሁሉ በላ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን ሞላ።
ማሕፀንን የሚከፍተውን ሁሉ ለይ፤ ከመንጋህና ከከብትህም መጀመሪያ የሚወለደው ተባት ለእግዚአብሔር ይሆናል።
እኔ ድካምን ሁሉና የብልሃት ሥራውን ተመለከትሁ፥ ለሰውም በባልንጀራው ዘንድ ቅንአትን እንዲያስነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው ተደነቁ፤ በግምባራቸውም ወደቁ።
ሙሴም እጅግ አዘነ፤ እግዚአብሔርንም አለው፥ “ወደ መሥዋዕታቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንዳችም ተመኝቼ አልወሰድሁም፤ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም።”
ለእግዚአብሔር ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከስንዴም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤
ነገር ግን የላሞቹን በኵራት፥ ወይም የበጎቹን በኵራት፥ የፍየሎችንም በኵራት አትቤዥም፤ ቅዱሳን ናቸውና፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፤ ስባቸውንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን መሥዋዕት ታደርገዋለህ።
አቤል ከቃኤል ይልቅ የሚበልጥ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፤ በዚህም ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ምስክሩም መሥዋዕቱን በመቀበል እግዚአብሔር ነው። በዚህም ከሞተ በኋላ እንኳ ተናገረ።
የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ ያለውን በትሩን ዘርግቶ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ አስነካ፤ እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥታ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ በላች። የእግዚአብሔርም መልአክ ከዐይኖቹ ተሰወረ።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።