Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 15:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ነበ​ል​ባል መጣ፤ የእ​ሳት መብ​ራ​ትና የሚ​ጤስ ምድ​ጃም መጣ፤ በዚ​ያም በተ​ከ​ፈ​ለው መካ​ከል አለፈ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና ታየ፤ በተከፈለውም ሥጋ መካከል ዐለፈ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፥ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ፀሐይ ጠልቃ በጨለመ ጊዜ የምድጃ እሳት ጢስና ነበልባል ታየ፤ በተቈራረጠውም ሥጋ መካከል አለፈ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 15:17
13 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ሁም እነ​ዚ​ህን ሁሉ ወሰ​ደ​ለት፤ በየ​ሁ​ለ​ትም ከፈ​ላ​ቸው፤ የተ​ከ​ፈ​ሉ​ት​ንም በየ​ወ​ገኑ ትይዩ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወፎ​ችን ግን አል​ቈ​ረ​ጣ​ቸ​ውም።


ከቍ​ጣው ጢስ ወጣ፤ ከአ​ፉም የሚ​በላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእ​ርሱ ተቃ​ጠለ።


እሳ​ትም ከሰ​ማይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወረ​ደች፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ እን​ጨ​ቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም በላች፤ በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ያለ​ውን ውኃ፥ አፈ​ሩ​ንም ላሰች።


ዳዊ​ትም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጠራ፤ ከሰ​ማ​ይም ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ በእ​ሳት መለ​ሰ​ለት፤ እሳ​ቱም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በላ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት ስለ ወረ​ደ​በት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም ሁሉ እጅግ ይና​ወጥ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጽ​መው ደነ​ገጡ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ነጐ​ድ​ጓ​ዱ​ንና መብ​ረ​ቁን፥ የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ፥ ተራ​ራ​ው​ንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው ርቀው ቆሙ።


ጽድቄ እንደ ብር​ሃን፥ ማዳ​ኔም እን​ደ​ሚ​በራ ፋና እስ​ኪ​ወጣ ድረስ ስለ ጽዮን ዝም አል​ልም፤ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጸጥ አል​ልም።


ከግ​ብፅ ሀገር ከብ​ረት ምድጃ ባወ​ጣ​ኋ​ቸው ቀን ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ያዘ​ዝ​ሁ​ትን፥ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ርጉ፤ እን​ዲ​ሁም እና​ንተ ሕዝብ ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ” ያል​ሁ​ትን ቃሌን ስሙ።


እና​ን​ተን ግን እንደ ዛሬው ሁሉ የር​ስቱ ሕዝብ ትሆ​ኑ​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስዶ ከብ​ረት እቶን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ችሁ።


ነበ​ል​ባ​ሉም ከመ​ሠ​ዊ​ያዉ ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ ነበ​ል​ባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑ​ሄና ሚስ​ቱም ተመ​ለ​ከቱ፤ በም​ድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በእጁ ያለ​ውን በት​ሩን ዘር​ግቶ ሥጋ​ዉ​ንና የቂ​ጣ​ዉን እን​ጎቻ አስ​ነካ፤ እሳ​ትም ከድ​ን​ጋዩ ውስጥ ወጥታ ሥጋ​ዉ​ንና የቂ​ጣ​ዉን እን​ጎቻ በላች። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከዐ​ይ​ኖቹ ተሰ​ወረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos