ዘፍጥረት 36:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዓናን ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ዲሶን፤ የዓናን ሴት ልጅ ኤሌባማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዓና ልጆች፦ ዲሶንና የዓና ሴት ልጅ ኦሆሊባማ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዓና ልጅ ዲሾን የተባለው ነው፤ ሴት ልጁም ኦሆሊባማ ትባላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዐናም ልጅ ዲሾን የተባለው ነው፤ ሴት ልጁም ኦሆሊባማ ትባላለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዓና ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ዲሶን፥ አህሊባማም የዓን ሴት ልጅ። |
የዔሳው ሚስት የኤሌባማ ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ ዮሔል መስፍን፥ ይጉሜል መስፍን፥ ቆሬ መስፍን፤ የዔሳው ሚስት የሐና ልጅ የኤሌባማ ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው።
ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ የኬጤያዊውን የዔሎን ልጅ ሐዳሶን፥ የኤውያዊው የሴቤሶ ልጅ ሐና የወለዳትን ኤሌባማን፥
የሳባቅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ኢኣ፥ ዓናን፤ ይህም ዓናን በምድረ በዳ የአባቱን የሳባቅን አህዮች ሲጠብቅ ፍል ውኃዎችን ያገኘ ነው።