ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊው የብኤልን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊው የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤
ዘፍጥረት 36:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሲም፥ ሞዛህ፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የራጉኤል ወንዶች ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህ ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የረዑኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፦ ናሐት፥ ዘራሕ፥ ሻማና ሚዛ፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት ባሴማት ልጆች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የረዑኤል ልጆች፦ ናሐት፥ ዘራሕ፥ ሻማና ሚዛ ናቸው፤ እነዚህም ዔሳው ባሴማት ከምትባለው ሚስቱ የወለዳቸው የልጅ ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የራጉኤልም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሣማ፥ ሚዛህ እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው። |
ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊው የብኤልን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊው የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤
ቴምናሕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ ዕቅብት ነበረች፤ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት፤ የዔሳውም ሚስት የሐዳሶ ልጆች እነዚህ ናቸው።
የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ ናሖት መስፍን፥ ዛራ መስፍን፥ ሲን መስፍን፥ ሞዛህ መስፍን፤ በኤዶም ምድር የራጉኤል ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው።