ዘፍጥረት 33:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፤ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ፤ ሰዎችም በአንድ ወይም በሁለት ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደ ሆነ ከብቶቹ ሁሉ ይሞታሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ግን እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ፣ እንደምታየው ልጆቹ ይህን ያህል የጠኑ አይደሉም፣ ለሚያጠቡት በጎችና ጥገቶች እንክብካቤ ማድረግ አለብኝ፤ እንስሳቱ ለአንዲት ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ በሙሉ ያልቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፥ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ መጠንቀቅ ይኖርብኛል፤ ሰዎችም አንድ ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደሆነ እንሰሶቹ ሁሉ ይሞታሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም እንዲህ አለ፤ “ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ጌታዬ ታውቃለህ፤ ለሚያጠቡት እንስሶች፥ ለግልገሎቻቸውና ለእንቦሶቻቸው መጠንቀቅ ይኖርብኛል፤ ለአንድ ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ እንስሶቹ በሙሉ ያልቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም አለው፦ ጌታዬ ሆይ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ ሰዎችም አንድ ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደ ሆን ከብቶቹ ሁሉ ይሞታሉ። |
ጌታዬ ከአገልጋዩ ፊት ቀድሞ ይለፍ፤ እኛም እንደ ቻልን እንሄዳለን፤ በጎዳናም እንውላለን፤ ወደ ጌታችን ወደ ሴይር እስክንደርስም በሕፃናቱ ርምጃ መጠን እንሄዳለን” አለው።
ዳዊትም፥ “ልጄ ሰሎሞን ታናሽና ለጋ ብላቴና ነው፤ ለእግዚአብሔርም የሚሠራው ቤት እጅግ ማለፊያና በሀገሩ ሁሉ ስሙና ክብሩ እንዲጠራ ይሆን ዘንድ ይገባል፤ ስለዚህ አዘጋጅለታለሁ” አለ። ዳዊትም ሳይሞት አስቀድሞ ብዙ አዘጋጀ።
ፍልስጥኤማውያንም እንዲሁ አደረጉ፤ የሚያጠቡትን ሁለቱን ላሞች ወሰዱ፤ በሰረገላውም ጠመዱአቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ዘጉባቸው፤