መንጎቹንም ለየብቻ ከፍሎ ለብላቴኖቹ ሰጣቸው፤ ብላቴኖቹንም፥ “በፊቴ እለፉ፤ መንጋውን ከመንጋው አርቁ” አላቸው።
ዘፍጥረት 32:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፊተኛውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “ወንድሜ ዔሳው ያገኘህ እንደ ሆነ፦ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለሀ? በፊትህ ያለው ይህስ መንጋ የማን ነው?’ ብሎ የጠየቀህም እንደሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀድሞ የሚሄደውንም እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ዔሳው አግኝቶህ፣ ‘የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? የምትነዳውስ ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፊተኛውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “ወንድሜ ዔሳው ያገኘህ እንደሆነ፥ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? በፊትህ ያለው ይህስ የማን ነው?’ ብሎ የጠየቀህም እንደሆነ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያዎቹንም እረኞች እንዲህ በማለት አዘዛቸው፤ “ወንድሜ ዔሳው በመንገድ አግኝቶ ‘የማን ሰዎች ናችሁ? ወዴትስ ትሄዳላችሁ? እነዚህ የምትነዱአቸው ከብቶች የማን ናቸው?’ ብሎ የጠየቃችሁ እንደ ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፊተኛውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ወንድሜ ዔሳው ያገኘህ እንደሆነ፦ አንተ የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? በፊትህ ያለው ይህስ የማን ነው? ብሎ የጠየቀህም እንደ ሆነ፥ |
መንጎቹንም ለየብቻ ከፍሎ ለብላቴኖቹ ሰጣቸው፤ ብላቴኖቹንም፥ “በፊቴ እለፉ፤ መንጋውን ከመንጋው አርቁ” አላቸው።
በዚያ ጊዜ አንተ፦ ‘ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የላከው የአገልጋይህ የያዕቆብ ነው፤ እርሱም ደግሞ እነሆ ከኋላችን ተከትሎናል’ በለው።”