La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 31:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ላባም ለያ​ዕ​ቆብ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ለት፥ “ሴቶቹ ልጆች ልጆች ናቸው፤ ወን​ዶ​ቹም ልጆች ልጆች ናቸው፤ መን​ጎ​ቹም ከብ​ቶች ናቸው፤ ይህ የም​ታ​የው ሁሉ የእኔ ነው፤ የል​ጆ​ችም ሀብት ነው፤ ዛሬም በእ​ነ​ዚህ በሴ​ቶች ልጆ​ችና በወ​ለ​ዱ​አ​ቸው ልጆ​ቻ​ቸው ላይ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ላባም ለያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ሴቶቹም፣ ልጆቹም የእኔው ልጆች ናቸው፣ መንጎቹም ቢሆኑ የራሴ ናቸው። ታዲያ፣ በእነዚህ ሴቶች ልጆቼና በወለዷቸው ልጆቻቸው ላይ ዛሬ ምን ማድረግ እችላለሁ?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ላባም ለያዕቆብ መልሶ እንዲህ አለው፥ “ሴቶቹ ልጆች ልጆቼ ናቸው፥ ሕፃናቱም ሕፃናቴ ናቸው፥ መንጎቹም መንጎቼ ናቸው፥ የምታየውም ሁሉ የእኔ ነው። ነገር ግን ዛሬ በእነዚህ በሴቶች ልጆቼና በወለዱአቸው ልጆቻቸው ላይ ምን ላደርግ እችላለሁ?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ላባም ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “እነዚህ ሴቶች የእኔ ልጆች ናቸው፤ ልጆቻቸውም የእኔው ናቸው፤ እነዚህም መንጋዎች የእኔ ናቸው፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ የምታየው ሁሉ የራሴ ነው፤ ነገር ግን ልጆቼንም ሆነ ልጆቻቸውን ለማስቀረት ምንም ማድረግ አልቻልኩም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ላባም እንዲህ ብሎ ለያቆብ መለሰለት፦ ሴቶቹ ልጆች ልጆቼ ናቸው ሕፃናቴ ናቸው፥ መንጎቹም መንጎቼ ናቸው የምታየውም ሁሉ የእኔ ነው ዛሬም በእነዚህ በሴቶች ልጆቼና በወለዱአቸው ልጆቻቸው ላይ ምን ላደርግ ይቻላል?

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 31:43
3 Referencias Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም የላባ ልጆች ያሉ​ትን ነገር፥ “ያዕ​ቆብ ለአ​ባ​ታ​ችን የሆ​ነ​ውን ሁሉ ወሰደ፤ ይህ​ንም ሁሉ ክብር ከአ​ባ​ታ​ችን ከብት አገኘ” ሲሉ ሰማ።


ላባም ማልዶ ተነ​ሥቶ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን ልጆ​ቹን ሳመ፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም፤ ላባም ተመ​ልሶ ወደ ስፍ​ራው ሄደ።


ወን​ዶች ልጆ​ቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ። ኀዘ​ኑ​ንም ያስ​ተ​ዉት ዘንድ አባ​ታ​ቸ​ውን ማለ​ዱት። ኀዘ​ኑ​ንም መተ​ውን እንቢ አለ፥ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃ​ብር እያ​ዘ​ንሁ እወ​ር​ዳ​ለሁ።” አባ​ቱም ስለ እርሱ አለ​ቀሰ።