ዘፍጥረት 31:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም አለ፥ “አምላኮችህን የምታገኝበት ሰው ግን እርሱ ይሙት፤ ገንዘብህም በእኔ ዘንድ ካለ በወንድሞቻችን ፊት እይ፤ ለአንተም ውሰደው” አለ። ያዕቆብ ሚስቱ ራሔል እንደ ሰረቀቻቸው አያውቅም ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ከእኛ መካከል የአንተን የጣዖታት ምስል ደብቆ የተገኘ ሰው ካለ ይሙት። ያንተ የሆነ አንዳች ነገር ከኔ ዘንድ ቢገኝ፣ አንተው ራስህ ዘመዶቻችን ባሉበት ፈልግና ውሰድ።” ይህን ሲል፣ ራሔል የጣዖታቱን ምስል መስረቋን ያዕቆብ አያውቅም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላኮችህን የምታገኝበት ሰው ግን እርሱ ይሙት፥ የአንተ የሆነውም በእኔ ዘንድ ይገኝ እንደሆነ በዘመዶቻችን ፊት ፈልግ፥ ውሰደውም” አለ። ያዕቆብ ራሔል እንደ ሰረቀቻቸው አያውቅም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእኛ መካከል የአንተ ጣዖቶች የተገኙበት ሰው ቢኖር ግን ይሙት፤ እነሆ፥ አሁን ዘመዶቻችንን ምስክር በማድረግ የአንተ የሆነውን ነገር ሁሉ ፈልገህ ውሰድ” አለው፤ ያዕቆብ ይህን ያለው ራሔል የአባቷን ጣዖቶች ሰርቃ እንደ ወሰደች ስላላወቀ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላኮችህን የምታገኝበት ሰው ግን እርሱ ይሙት የአንተ የሆነውም በእኔ ዘንድ ይገኝ እንደ ሆነ በወንድሞቻችን ፊት ፈልግ ለአንተም ውሰደው አለ። ራሔል እንደ ሰረቀቻቸው ያዕቆብ አያውቅም ነበርና። |
ስለዚህም በፊትህ ያለውን ደመወዜን ለመመልከት በመጣህ ጊዜ ወደፊት ጻድቅነቴን ይመሰክርልኛል፤ ከፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ የሌለበት፥ ከበግ ጠቦቶችም ጥቁር ያልሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰረቀ ይቈጠርብኝ።”
ያዕቆብም መለሰ፤ ላባንም እንዲህ አለው፥ “ልጆችህንና ገንዘቤን ሁሉ ከእኔ የምትቀማኝ ስለመሰለኝና ስለፈራሁ ይህን አደረግሁ።”
ላባም ወደ ያዕቆብ ድንኳንና ወደ ልያም ድንኳን ገባና በረበረ፤ አላገኘምም፤ ከዚያም ወጣና ወደ ሁለቱ ዕቁባቶቹ ድንኳን ገባ፤ ነገር ግን አላገኘም። ወደ ራሔልም ድንኳን ገባ።