ላባም ያዕቆብን አለው፥ “ለምን እንዲህ አደረግህ? ከእኔ በስውር የኰበለልህ? ልጆችንስ ሰርቀህ በሰይፍ እንደማረከ የወሰድኻቸው?
ዘፍጥረት 31:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብትነግረኝ ኑሮ በደስታና በሐሴት፥ በዘፈን፥ በከበሮና በበገና በሸኘሁህ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ ለምን ተደብቀህ ሄድህ? ለምንስ አታለልኸኝ? ብትነግረኝ ኖሮ፣ በደስታና በዘፈን በከበሮና በበገና አልሸኝህም ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለምን በስውር ሸሸህ፥ እኔንም አታለልከኝ፥ በደስታና በዘፈንም በከበሮና በበገና እንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳትነግረኝ ተሰውረህ በመሄድ ለምን አታለልከኝ? ነግረኸኝ ቢሆን ኖሮ በከበሮና በመሰንቆ እየተዘፈነ በደስታ በሸኘሁህ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለምን በስውር ሸሸህ? ከእኔም ከድተህ ስለምን ኮበለልህ? በደስታና በዘፈም በከበሮና በበገና እንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም? |
ላባም ያዕቆብን አለው፥ “ለምን እንዲህ አደረግህ? ከእኔ በስውር የኰበለልህ? ልጆችንስ ሰርቀህ በሰይፍ እንደማረከ የወሰድኻቸው?
ያዕቆብም መለሰ፤ ላባንም እንዲህ አለው፥ “ልጆችህንና ገንዘቤን ሁሉ ከእኔ የምትቀማኝ ስለመሰለኝና ስለፈራሁ ይህን አደረግሁ።”
በመሰንቆና በበገና፥ በከበሮና በእምቢልታም እየዘፈኑ የወይን ጠጅን ይጠጣሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፤ የእጁንም ሥራ አላስተዋሉም።
ጌዴዎንም ከባሪያዎቹ ዐሥራ ሦስት ሰዎችን ወስዶ እግዚአብሔር እንዳለው አደረገ፤ የአባቱንም ቤተ ሰቦች፥ የከተማዉንም ሰዎች ስለፈራ ይህን በቀን ለማድረግ አልቻለም፤ ነገር ግን በሌሊት አደረገው።