ሎሌውም ከጌታው ግመሎች መካከል ዐሥር ግመሎችን ወስዶ፥ ከጌታውም ዕቃ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ፤ ተነሥቶም ወደ ሦርያ ወንዞች መካከል ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።
ዘፍጥረት 31:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ተነሣ፤ ልጆቹንና ሚስቶቹንም በግመሎች ላይ አስቀመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ያዕቆብ ልጆቹንና ሚስቶቹን ግመሎች ላይ አስቀመጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ያዕቆብ ተነሣ፥ ልጆቹንና ሚስቶቹንም በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም ተነሥቶ ልጆቹንና ሚስቶቹን በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ተነሣ ልጆቹንና ሚስቶቹንም በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤ |
ሎሌውም ከጌታው ግመሎች መካከል ዐሥር ግመሎችን ወስዶ፥ ከጌታውም ዕቃ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ፤ ተነሥቶም ወደ ሦርያ ወንዞች መካከል ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።
ርብቃም ተነሣች፤ ደንገጥሮችዋም፥ በግመሎችዋ ላይ ተቀምጠው ከሰውዬው ጋር አብረው ሄዱ፤ ሎሌውም ርብቃን ተቀብሎ ሄደ።
ስለዚህም እግዚአብሔር ከአባታችን የነሣው ይህ ሁሉ ሀብትና ክብር ለእኛና ለልጆቻችን ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ አድርግ።”
መንጎቹንም ሁሉ፥ የቤቱንም ዕቃ ሁሉ፥ በሁለቱ ወንዞች መካከል ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ።
ዳዊትም ሄዶ የአጥቢያ ኮከብ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግመኛም በማግሥቱ መታቸው፤ ከእነርሱም በግመል ተቀምጠው ከሸሹት አራት መቶ ጐልማሶች በቀር አንድም ያመለጠ የለም።