አብራምም በከነዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከተቀመጠ በኋላ፥ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋን አጋርን ወስዳ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።
ዘፍጥረት 30:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም መውለድን እንዳቆመች በአየች ጊዜ አገልጋይዋን ዘለፋን ወሰደች፤ ሚስት ትሆነውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው፤ ያዕቆብም ወደ እርስዋ ገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያም ልጅ መውለድ ማቆሟን እንደ ተረዳች፣ አገልጋይዋን ዘለፋን ሚስት እንድትሆነው ለያዕቆብ ሰጠችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም መውለድን እንዳቆመች ባየች ጊዜ ባርያዋን ዘለፋን ወሰደች፥ ሚስት ትሆንውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልያም መውለድ እንዳቆመች በተገነዘበች ጊዜ አገልጋይዋን ዚልፋን እንደ ሚስት አድርጋ ለያዕቆብ ሰጠችው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም መውለድን እንዳቆመች ባየች ጊዜ ባሪያዋን ዘለፋን ወሰደች፥ ሚስት ትሆንውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው። |
አብራምም በከነዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከተቀመጠ በኋላ፥ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋን አጋርን ወስዳ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።
ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ በዚህም ጊዜ “እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።
በዚያችም ሌሊት ከእርስዋ ጋር አደረ። እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፤ ፀነሰችም፤ አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች።
ራሔልም፥ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገኝ፤ ብርቱ ትግልንም ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፤ አሸነፍሁም፤ እኅቴንም መሰልኋት” አለች፤ ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።