እንደዚህ በልቡ ያሰበውን መናገሩን ሳይፈጽም እንዲህ ሆነ፦ የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት የሚልካ ልጅ የባቱኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እንስራዋንም በጫንቃዋ ተሸክማ ነበር።
ዘፍጥረት 29:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ፥ የላባ ልጅ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ደረሰች፤ እርስዋ የአባቷን በጎች ትጠብቅ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ከእረኞቹ ጋራ በመነጋገር ላይ ሳለ፣ ራሔል፣ እረኛ ነበረችና የአባቷን በጎች እየነዳች መጣች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ የላባ ልጅ ራሔል ከአባትዋ በጎች ጋር ደረሰች፥ እርሷ የአባትዋን በጎች ትጠብቅ ነበርና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም ከእረኞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ወደዚያ መጣች፤ እርስዋ የበጎች እረኛ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ የላባ ልጅ ራሔል ከአባትዋ በጎች ጋር ደረስች እርስዋ የአባትዋን በጎች ትጠብቅ ነበርና። |
እንደዚህ በልቡ ያሰበውን መናገሩን ሳይፈጽም እንዲህ ሆነ፦ የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት የሚልካ ልጅ የባቱኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እንስራዋንም በጫንቃዋ ተሸክማ ነበር።
ያዕቆብም የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የአጎቱን የላባን በጎች በአየ ጊዜ ቀረበ፤ ከጕድጓዱም አፍ ድንጋዩን አነሣ፤ የአጎቱን የላባን በጎችም አጠጣ።
እነርሱም አሉ፥ “እረኞች ሁሉ ካልተሰበሰቡና ድንጋዪቱን ከጕድጓዱ አፍ ካላነሡአት በቀር አንችልም፤ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።”