መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተሰበሰቡ ጊዜ እረኞች ድንጋይዋን ከጕድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር፤ ድንጋይዋንም ወደ ስፍራው መልሰው በጕድጓዱ አፍ እንደገና ይገጥሙት ነበር።
ዘፍጥረት 29:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም አሉ፥ “እረኞች ሁሉ ካልተሰበሰቡና ድንጋዪቱን ከጕድጓዱ አፍ ካላነሡአት በቀር አንችልም፤ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “መንጎቹ ሁሉ ተሰብስበው ድንጋዩ ከጕድጓዱ አፍ ካልተንከባለለ በቀር አንችልም፤ ከዚያም በጎቹን እናጠጣቸዋለን” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም አሉ፦ “መንጎች ሁሉ እስኪከማቹና ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም፥ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን ይዘው እዚህ ከመሰብሰባቸው በፊት ምንም ማድረግ አንችልም፤ ሁሉም እዚህ ከመጡ በኋላ ግን ድንጋዩን በኅብረት አንከባለን በጎቹን እናጠጣቸዋለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም አሉ፦ መንጎች ሁሉ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም ከዚይም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን። |
መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተሰበሰቡ ጊዜ እረኞች ድንጋይዋን ከጕድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር፤ ድንጋይዋንም ወደ ስፍራው መልሰው በጕድጓዱ አፍ እንደገና ይገጥሙት ነበር።
እርሱም፥ “ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብቶቹ የሚሰበሰቡበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም፤ አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩአቸው” አላቸው።
እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ፥ የላባ ልጅ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ደረሰች፤ እርስዋ የአባቷን በጎች ትጠብቅ ነበርና።
የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊም እንዲህ አሉአቸው፥ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ለመስጠት ይህን ነገር እናደርግ ዘንድ አይቻለንም፤ ይህ ነውር ይሆንብናልና።
ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ፤ ለእነርሱም ለብቻቸው፤ ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው፤ የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይችሉምና፥ ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና።