ዘፍጥረት 27:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያደረግህበትንም እስኪረሳው ድረስ፤ በአንድ ቀን ሁለታችሁን እንዳላጣ፥ ከዚያም ልኬ አመጣሃለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ቍጣው በርዶለት ያደረግህበትን ከረሳ በኋላ፣ እንድትመለስ እልክብህና ትመጣለህ። ሁለታችሁንም በአንድ ቀን ለምን ልጣ?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድምህ ቁጣ ከአንተ እስኪመለስ ድረስ፥ ያደረግህበትንም እስኪረሳው ድረስ፥ ከዚያም ልኬ አስመጣሃለሁ፥ በአንድ ቀን ሁለታችሁን ለምን አጣለሁ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቊጣውም ሲበርድ ያደረግህበትን ነገር ይረሳል፤ ከዚያ በኋላ ሰው ልኬ አስመጣሃለሁ፤ ለምን ሁለታችሁንም በአንድ ቀን ልጣ?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድምህ ቍጣ ከአንተ እስኪመለስ ድረስ፥ ያደረግህባትንም እስኪረሳው ድረስ ከዚይም ልኬ አስመጣሃለሁ በአንድ ቀን ሁለታችሁን ለምን አጣለሁ? |
ያዕቆብም አባቱን አለው፥ “የበኵር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፤ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፤ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና ብለህ ተቀመጥ፤ ካደንሁትም ብላ።”
አረማውያንም እፉኝቱ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመስላል፤ ከባሕር እንኳ በደኅና ቢወጣም በሕይወት ይኖር ዘንድ የእግዚአብሔር ፍርድ አልተወውም” አሉ።