እግዚአብሔርም አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይወለዳሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
ዘፍጥረት 27:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው፥ “እነሆ ጌታህ አደረግሁት፤ ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች አደረግኋቸው፤ እህሉን፥ ወይኑንና ዘይቱንም አበዛሁለት፤ ለአንተ ግን፥ ልጄ ሆይ፥ ምን ላድርግልህ?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅም ለዔሳው፣ “በአንተ ላይ የበላይነት እንዲኖረው፣ ወንድሞቹ ሁሉ አገልጋዮቹ እንዲሆኑ፣ እህሉ፣ የወይን ጠጁም የተትረፈረፈ እንዲሆንለት መርቄዋለሁ። ታዲያ ልጄ፣ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው፦ “እነሆ፥ ጌታህ አደረግሁት፥ ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች ይሆኑ ዘንድ ሰጠሁት፥ በእህልም በወይንም አበረታሁት፥ ለአንተ ግን፥ ልጄ ሆይ፥ ምን ላድርግ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅም “ቀደም ብዬ እርሱን የአንተ ጌታ አድርጌዋለሁ፤ ወንድሞቹ ሁሉ የእርሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጌአለሁ፤ እህልና የወይን ጠጅ እንዲበዛለት አድርጌአለሁ፤ ልጄ ሆይ! እንግዲህ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው፦ እነሆ ጌታህ አደረግሁት ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች ይሆኑ ዘንድ ሰጠሁት በእህልም በወይንም አበረታሁት ለአንተ ግን ልጄ ሆይ ምን ላድርግ? |
እግዚአብሔርም አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይወለዳሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
መላዋን ኤዶምያስን ይጠብቁ ዘንድ በኤዶምያስ ሁሉ ጭፍሮችን አኖረ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሚሄድበት ቦታ ሁሉ ጠበቀው።
ኢዮሣፍጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተርሴስ መርከብን ሠራ፤ ነገር ግን መርከቢቱ በጋሴዎንጋቤር ተሰብራለችና አልሄደችም።
እስራኤልም ተማምኖ፥ በያዕቆብ ምድር ብቻውን፥ በስንዴና በወይን ምድር ይኖራል፤ ሰማይ ከደመናና ከጠል ጋር ለአንተ ነው።