እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ ከአደንኸው እንድበላና ነፍሴ እንድትባርክህ አምጣልኝ” አለው። አቀረበለትም፤ በላም፤ ወይንም አመጣለት፤ እርሱም ጠጣ።
ዘፍጥረት 27:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱ ይስሐቅም፥ “ልጄ ሆይ፥ ወደ እኔ ቅረብ፤ ሳመኝም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አባቱ ይሥሐቅ፣ ያዕቆብን፣ “ልጄ ሆይ፤ እስኪ ቀረብ በልና ሳመኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቱ ይስሐቅም፦ “ልጄ ሆይ፥ ወደ እኔ ቅረብ ሳመኝም” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አባቱ ይስሐቅ “ልጄ ሆይ፥ ቀረብ በልና ሳመኝ” አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱ ይስሐቅም ልጄ ሆይ ወደ እኔ ቅረብ ሳመኝም አለው። |
እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ ከአደንኸው እንድበላና ነፍሴ እንድትባርክህ አምጣልኝ” አለው። አቀረበለትም፤ በላም፤ ወይንም አመጣለት፤ እርሱም ጠጣ።
ወደ እርሱም ቀረበ፤ ሳመውም፤ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፤ ባረከውም፤ እንዲህም አለ፥ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤
ኢዮአብም ወደ ንጉሥ መጥቶ ነገረው፤ አቤሴሎምንም ጠራው፥ ወደ ንጉሡም ገብቶ ሰገደለት፤ በንጉሡም ፊት ወደ ምድር በግንባሩ ወደቀ፤ ንጉሡም አቤሴሎምን ሳመው።