ዘፍጥረት 26:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፍ ከፍም አለ፤ እጅግም ታላቅ እስኪሆን ድረስ እየጨመረ ይበዛ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየውም እጅግ ባለጠጋ እስኪሆን ድረስ ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረለት ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባለ ጠጋ ሰውም ሆነ፥ እጅግ እስኪበልጥ ድረስም እየጨመረ ይበዛ ነበር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረለት ስለ ሄደ እጅግ ባለጸጋ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባለ ጠጋ ሰውም ሆነ እጅግ እስኪበልጥ ድረስም እየጨመተ ይበዛ ነበር፤ |
እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው፤ አገነነውም፤ ላሞችንና በጎችን፥ ወርቅንና ብርን፥ ወንዶች ባሪያዎችንና ሴቶች ባሪያዎችን፥ ግመሎችንና አህዮችንም ሰጠው።
ያዕቆብም እጅግ ባለጠጋ ሆነ፤ ሴቶችም ወንዶችም አገልጋዮች፥ ብዙ ከብትም፤ ላሞችም፥ በጎችም፥ ግመሎችና አህዮችም ሆኑለት።