ዘፍጥረት 25:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም ዔሳውን ይወድ ነበር፤ እርሱ ከአደነው ይበላ ነበርና። ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅ ከዐደን የመጣ ሥጋ ደስ ይለው ስለ ነበር፣ ዔሳውን ይወድደው ነበር፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድደው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም ዔሳው ካደነው ይበላ ነበርና ይወደው ነበር፥ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሳው እያደነ ሥጋ ያበላው ስለ ነበረ ይስሐቅ ዔሳውን ይወድ ነበር። ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም ዔሳውን ይወድ ነበረ ካደነው ይበላ ነበርና፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበረች። |
ያዕቆብም አባቱን አለው፥ “የበኵር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፤ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፤ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና ብለህ ተቀመጥ፤ ካደንሁትም ብላ።”
እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ ከአደንኸው እንድበላና ነፍሴ እንድትባርክህ አምጣልኝ” አለው። አቀረበለትም፤ በላም፤ ወይንም አመጣለት፤ እርሱም ጠጣ።
እርሱም ደግሞ መብል አዘጋጀ፥ ለአባቱም አመጣ፤ አባቱንም፥ “አባቴ ተነሥ፤ ነፍስህም ትባርከኝ ዘንድ ልጅህ ከአደነው ብላ” አለው።
ወደ በጎቻችን ሄደህ ሁለት መልካም ጠቦቶች አምጣልኝ፤ እነርሱንም ለአባትህ እንደሚወደው መብል አደርጋቸዋለሁ፤