ዘፍጥረት 25:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ትውልድም ይህ ነው፤ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአብርሃም ልጅ የይሥሐቅ ትውልድ ይህ ነው። አብርሃም ይሥሐቅን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ትውልድም ይህ ነው፥ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ታሪክ ይህ ነው፤ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ትውልድም ይህ ነው አብርሃም ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነውም ርብቃን አገባ። |
ይስሐቅም ሚስት ትሆነው ዘንድ የሶርያዊውን የላባን እኅት፥ የሶርያዊውን የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ከሁለቱ ከሶርያ ወንዞች መካከል በወሰዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።
የአብርሃም ዕቅብት ኬጡራ የወለደችለት ልጆች፤ ዘምራን፥ ዮቅሳን፥ ሜዳም፥ ምድያን፥ ዮሳብቅ፥ ስዌሕ፥ የዮቅሳንም ልጆች፤ ሳባ፥ ዳዳን።
የግዝረትንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚህም በኋላ ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛው ቀንም ገረዘው፤ እንዲሁ ይስሐቅም ያዕቆብን፥ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የቀደሙ አባቶችን ገረዙ።