La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 24:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሴቲ​ቱም ከአ​ንተ ጋር ወደ​ዚች ምድር ለመ​ም​ጣት ባት​ፈ​ቅድ አንተ ከዚህ መሐላ ንጹሕ ነህ፤ ልጄን ግን ወደ​ዚያ እን​ዳ​ት​መ​ል​ሰው ተጠ​ን​ቀቅ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሴቲቱ ዐብራህ ወደዚህ ለመምጣት ፈቃደኛ ካልሆነች ግን ካስማልሁህ መሐላ ነጻ ትሆናለህ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትውሰደው” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሴቲቱም ከአንተ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደሆነ ከዚህ ካቀረብሁህ መሐላ ንጹሕ ነህ፥ ልጄን ግን ወደዚያ አትመልሰው።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ልጅትዋ ከአንተ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆን ከዚህ መሐላ ነጻ ትሆናለህ፤ ልጄን ግን በምንም ዐይነት ወደዚያ አትመልሰው።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሴቲቱም ከአንተ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደ ሆነ ከዚህ ካቀረብሁህ መሐላ ንጽሕ ነህ፤ ልጄን ግን ወደዚያ አትመልሰው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 24:8
8 Referencias Cruzadas  

የዚ​ያን ጊዜ ከመ​ሐ​ላዬ ንጹሕ ትሆ​ና​ለህ፤ ወደ ዘመ​ዶች ሄደህ እነ​ርሱ ባይ​ሰ​ጡህ ካማ​ል​ሁህ መሐላ ንጹሕ ትሆ​ና​ለህ።”


አባቷ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስእ​ለቷ፥ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐ​ላዋ አይ​ጸ​ኑም፤ አባቷ ከል​ክ​ሎ​አ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ይላ​ታል።


ባልዋ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስእ​ለ​ቷና ራስ​ዋን ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ አይ​ጸ​ኑም፤ ባልዋ ከል​ክ​ሎ​አ​ታ​ልና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይቅር ይላ​ታል።


እው​ነ​ት​ንም ታው​ቋ​ታ​ላ​ችሁ፤ እው​ነ​ትም አር​ነት ታወ​ጣ​ች​ኋ​ለች።”


እር​ሱም እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንና አባ​ቶ​ቻ​ችን ሆይ፥ ስሙ፤ የክ​ብር አም​ላክ ለአ​ባ​ታ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃም በሁ​ለት ወን​ዞች መካ​ከል ሳለ ወደ ካራ​ንም ሳይ​መጣ ተገ​ለ​ጠ​ለት።


ስለ​ማ​ል​ን​ላ​ቸው መሐላ ጥፋት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብን ይህን አና​ድ​ር​ግ​ባ​ቸው፤ በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ተ​ዋ​ቸው፤ እን​ግ​ዛ​ቸ​ውም” አሉ​አ​ቸው።