ዐይኑንም በአነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤
ዘፍጥረት 23:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም በሀገሩ ሕዝብ ሁሉ ፊት ሰገደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃም እንደ ገና የአገሬውን ሕዝብ እጅ ነሣና መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት እጅ ነሣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃም ግን በሒታውያን ፊት እንደገና እጅ ነሣና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ፤ |
ዐይኑንም በአነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤
ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰዶም ከተማ በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ወደ ምድር ደፍቶ ሰገደላቸው፤
“አይደለም፥ ጌታዬ፥ ቀርበህ ስማኝ፤ እርሻውን፥ በውስጡም ያለውን ዋሻውን ሰጥቼሃለሁ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼሃለሁ፤ ሬሳህን ቅበር።”
የሀገሩ ሕዝብም ሲሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “ከእኔ ቅርብ ነህና ስማኝ፤ የእርሻህንም ዋጋ ከእኔ ውሰድ፤ ሬሳዬንም በዚያ እቀብራለሁ።”