ዘፍጥረት 21:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሣራም ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን ልጅ ይስማኤልን ከልጅዋ ከይስሐቅ ጋር ሲጫወት አየችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሌላ በኩል ደግሞ፣ ግብጻዊቷ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል በይሥሐቅ ላይ ሲያሾፍበት ሣራ አየች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሣራም ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን ልጅ ሲስቅ አየችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል ከዕለታት አንድ ቀን ሣራ ከልጅዋ ከይስሐቅ ጋር ሲጫወት አየችው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሣራም ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን ልጅ ሲስቅ አየችው። |
ከዚህም በኋላ አጋር ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን የሕፃኑን ስም ይስማኤል ብሎ ጠራው።
ስለ ይስማኤልም እነሆ፥ ሰምቼሃለሁ፤ እባርከዋለሁ፤ አበዛዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ ዐሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፤ ታላቅ ሕዝብም አደርገዋለሁ።
መልእክተኞቹም ከከተማ ወደ ከተማ በኤፍሬምና በምናሴ ሀገር እስከ ዛብሎን ሄዱ፤ እነዚያ ግን በንቀት ሳቁባቸው፤ አፌዙባቸውም።
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ ለመዘባበት በእኔ ላይ ሳቁ፤ አባቶቻቸውን የናቅሁባቸውና እንደ መንጋዬ ውሾች ያልቈጠርኋቸው ዛሬ ለብቻቸው ይገሥጹኛል።
ዛይ። ኢየሩሳሌም ቀድሞ ወድዳ በሠራችው ሥራ ሁሉ የመከራዋን ወራት አሰበች፤ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ፥ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት፤ በመፍረስዋም ሳቁ።