ዘፍጥረት 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ላይ እንቅልፍን አመጣ፤ አንቀላፋም ፤ ከጎኑም አጥንቶች አንድ አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ መላው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐድኑ አንዲት ዐጥንት ወስዶ፣ ስፍራውን በሥጋ ሞላው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርም አዳምን ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጎኑ አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐኑ አጥንቶች አንዱን ወሰደና ባዶውን ቦታ በሥጋ ሞላው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፤ አንቀላዳም ከጎኑም አንዲት እጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። |
ዳዊትም በሳኦል ራስጌ የነበረውን ጦርና የውኃውን መንቀል ወሰደ፤ ወደ ቤታቸውም ተመለሱ። ማንም ያየ አልነበረም፤ ያወቃቸውም ማንም አልነበረም፤ የነቃም ማንም አልነበረም፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ እንቅልፍ ወድቆባቸው ነበርና ሁሉ ተኝተው ነበር።