እነዚያም መላእክት ሎጥን አሉት፥ “ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማችም ቢሆን፥ ወንድ ልጅም ቢሆን፥ ሴት ልጅም ብትሆን፥ በዚህ ከተማ የምታውቀው ወዳጅ ቢኖርህ ያለህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስወጣቸው፤
ዘፍጥረት 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስክ ታላቃቸው ድረስ ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ ደጃፉንም ሲፈልጉ ደከሙ፤ አጡትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በሩን እንዳያገኙት በቤቱ ደጃፍ ላይ የተሰበሰቡትን ወጣቶችና ሽማግሌዎች ዐይን አሳወሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው፥ ሰዎቹም ደጃፉን ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ውጪ የነበሩት ወጣቶችና ሽማግሌዎች ሁሉ በሩን ማየት እንዳይችሉ ዐይናቸውን አሳወሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታለቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው ደጃፉንም ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ። |
እነዚያም መላእክት ሎጥን አሉት፥ “ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማችም ቢሆን፥ ወንድ ልጅም ቢሆን፥ ሴት ልጅም ብትሆን፥ በዚህ ከተማ የምታውቀው ወዳጅ ቢኖርህ ያለህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስወጣቸው፤
ወደ እርሱም በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ፥ “አቤቱ፥ እነዚህን ሰዎች አሳውራቸው” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ቃል አሳወራቸው።
በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፤ ዳግመኛም ጕልበት እያለኝ ከእንግዲህ ወዲህ ይህን መንገድ አልተውም አላልሽም፤ ይህንም ስላደረግሽ አላፈርሽም።
እነሆ፥ አሁን የእግዚአብሔር እጅ በአንተ ላይ ነው፤ ዕውርም ትሆናለህ፤ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” ወዲያውኑም ታወረ፤ ጨለማም ዋጠው፤ የሚመራውም ፈለገ።