ዘፍጥረት 15:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም እነዚህን ሁሉ ወሰደለት፤ በየሁለትም ከፈላቸው፤ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልቈረጣቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራምም እነዚህን ሁሉ አቀረበለት፤ ቈርጦም ሁለት ቦታ ከከፈላቸው በኋላ፣ እያንዳንዱን ክፍል በሌላው ወገን ትይዩ አስቀመጠ፤ ወፎችን ግን ለሁለት አልከፈላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፥ ወፎችን ግን አልከፈለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብራምም እነዚህን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር አምጥቶ እያንዳንዱን እየቈረጠ በሁለት ከፈለው፤ የተከፈሉትንም ትይዩ አድርጎ በሁለት መስመር አስቀመጣቸው። ወፎቹን ግን ቈርጦ አልከፈላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈለትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው ወፎችን ግን አልከፈለም። |
እንዲህም ሆነ፤ ፀሐይም በገባ ጊዜ ነበልባል መጣ፤ የእሳት መብራትና የሚጤስ ምድጃም መጣ፤ በዚያም በተከፈለው መካከል አለፈ።
እርሱም አለው፥ “የሦስት ዓመት ላም፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም አምጣ፤ እኒህንም ሁሉ አምጥተህ ከሁለት ከሁለት ቍረጣቸው፤ ወፎችን ግን አትቍረጣቸው።”
ከክንፎቹም ይሰብረዋል፤ ነገር ግን አይለየውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ያኖረዋል፤ መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።