አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።
ዘፍጥረት 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰዶምንና የገሞራን ፈረሶች ሁሉ፥ ስንቃቸውንም ሁሉ ይዘው ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አራቱ ነገሥታትም በሰዶምና በገሞራ ያገኙትን ሀብትና ምግብ ሁሉ ዘርፈው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰዶምንና የገሞራን ከብት ሁሉ መብላቸውንም ሁሉ ወስደው ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አራቱ ነገሥታት በሰዶምና በገሞራ ያገኙትን ነገር ሁሉ ምግብ እንኳ ሳይቀር ማርከው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰዶምንና የገሞራንን ከብት ሁሉ መብላቸውንም ሁሉ ወስደው ሄዱ። |
አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።
ያም የጨው ሸለቆ የዝፍት ጕድጓዶች ነበሩበት። የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤ የቀሩትም ወደ ተራራማው ሀገር ሸሹ።
በሬህ በፊትህ ይታረዳል፤ ከእርሱም አትበላም። አህያህ ከእጅህ በግድ ይወሰዳል፤ ወደ አንተም አይመለስም፤ በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚረዳህም አታገኝም።
እግዚአብሔር ልትድን በማትችልበት በክፉ ቍስል ጕልበትህንና ጭንህን ከእግርህ ጫማ እስከ አናትህ ድረስ ይመታሃል።
እስክትጠፋም ድረስ የከብትህን ፍሬ፥ የምድርህንም ፍሬ ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ እህልህን፥ ወይንህንም፥ ዘይትህንም፥ የላምህንና የበግህንም መንጋ አይተውልህም።