ዘፍጥረት 11:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታራንም ከወለደ በኋላ ናኮር መቶ ሀያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታራን ከወለደ በኋላ ናኮር 119 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታራንም ከወለደ በኋላ ናኮር መቶ ሃያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ 119 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታራንም ወለደ፤ ታራንም ከወለደ በኍላ ናኮር መቶ ሃያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ ወንዶችን ሴቶችንም ወለደ ሞተም። |
ጌታ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይላል፦ ዘርሽና ትውልድሽ ከከነዓን ምድር ነው፤ አባትሽ አሞራዊ ነበረ፤ እናትሽም ኬጢያዊት ነበረች።