ምድርም በየዘሩ፥ በየወገኑና በየመልኩ የሚዘራ ቡቃያን፥ በምድር ላይ በየወገኑ ዘሩ በውስጡ የሚገኘውንና ፍሬ የሚያፈራውን ዛፍ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ዘፍጥረት 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ። ሦስተኛም ቀን ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሸ፤ ነጋም፤ ሦስተኛ ቀን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሦስተኛ ቀን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ ሦስተኛ ቀን ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ሦስተኚ ቀን። |
ምድርም በየዘሩ፥ በየወገኑና በየመልኩ የሚዘራ ቡቃያን፥ በምድር ላይ በየወገኑ ዘሩ በውስጡ የሚገኘውንና ፍሬ የሚያፈራውን ዛፍ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
እግዚአብሔርም አለ፥ “በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በቀንና በሌሊትም ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች፥ ለዘመናት፥ ለዕለታት፥ ለዓመታትም ይሁኑ።
እግዚአብሔር ያን ጠፈር “ሰማይ” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ሁለተኛም ቀን ሆነ።