ቍጥራቸውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወርቅ ሳሕኖች፥ አንድ ሺህም የብር ሳሕኖች፥ ሃያ ዘጠኝም ቢላዋዎች፥ ሠላሳ የወርቅ ዳካዎች፥
ዕዝራ 8:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህናቱና ሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ይወስዱት ዘንድ ብሩንና ወርቁን፥ ዕቃዎቹንም በሚዛን ተቀበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ካህናቱና ሌዋውያኑ ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ አምላካችን ቤት እንዲሄድ የተመዘነውን ብር፣ ወርቅና ንዋያተ ቅድሳት ተረከቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱና ሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ለመውሰድ ብሩንና ወርቁን ዕቃዎቹንም በሚዛን ተቀበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ካህናቱና ሌዋውያኑ ብሩንና ወርቁን፥ ጠቅላላውንም ንዋያተ ቅድሳት ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ለመውሰድ ኀላፊነትን ተረከቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህናቱና ሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ይወስዱት ዘንድ ብሩንና ወርቁን፥ ዕቃዎቹንም በሚዛን ተቀበሉ። |
ቍጥራቸውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወርቅ ሳሕኖች፥ አንድ ሺህም የብር ሳሕኖች፥ ሃያ ዘጠኝም ቢላዋዎች፥ ሠላሳ የወርቅ ዳካዎች፥
ንጉሡንም፥ “የአምላካችን እጅ በሚሹት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፤ ኀይሉና ቍጣው ግን እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተናግረን ነበርና፤ በመንገድ ካለው ጠላት ያድኑን ዘንድ ጭፍራና ፈረሰኞች ከንጉሡ እለምን ዘንድ አፍሬ ነበርና።
በአራተኛውም ቀን ብሩና ወርቁ፥ ዕቃዎቹም በአምላካችን ቤት በካህኑ በኦርያ ልጅ በሜሪሞት እጅ ተመዘኑ፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ፤ ከእነርሱም ጋር ሌዋውያን የኢያሱ ልጅ ኢዮዛብድና የቤንዊ ልጅ ናሕድያ ነበሩ።