La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕዝራ 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ናቡ​ከ​ደ​ነ​ዖ​ርም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ካለው መቅ​ደስ ወስዶ ወደ ባቢ​ሎን ያመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የወ​ር​ቅና የብር ዕቃ ይሰጥ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወዳ​ለው መቅ​ደስ ወደ ስፍ​ራው ይወ​ሰድ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ይኑር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲሁም ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከሚገኘው ቤተ መቅደስ አውጥቶ ወደ ባቢሎን የወሰዳቸው የእግዚአብሔር ቤት የወርቅና የብር ዕቃዎች፣ በኢየሩሳሌም ወዳለው ቦታቸው ወደ ቤተ መቅደሱ እንዲመለሱ ይሁን፤ በእግዚአብሔርም ቤት ይቀመጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ናቡከደነፆርም በኢየሩሳሌም ካለው መቅደስ ወስዶ ወደ ባቢሎን ያመጣው የእግዚአብሔር ቤት የወርቅና የብር ዕቃዎች ይመለስ፥ በኢየሩሳሌምም ወዳለው መቅደስ ወደ ስፍራው ይወሰድ፥ በእግዚአብሔር ቤት ይኑር።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲሁም ከዚህ በፊት ንጉሥ ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ ማርኮ ያወጣቸው ከወርቅና ከብር የተሠሩትም ንዋያተ ቅድሳት ወደዚያው ተመልሰው በኢየሩሳሌም በሚሠራው ቤተ መቅደስ በተገቢ ቦታቸው ይቀመጡ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ናቡከደነፆርም በኢየሩሳሌም ካለው መቅደስ ወስዶ ወደ ባቢሎን ያመጣው የእግዚአብሔር ቤት የወርቅና የብር ዕቃ ይመለስ፤ በኢየሩሳሌምም ወዳለው መቅደስ ወደ ስፍራው ይወሰድ፤ በእግዚአብሔር ቤት ይኑር።

Ver Capítulo



ዕዝራ 6:5
12 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤተ መዛ​ግ​ብት ከዚያ አወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ የሠ​ራ​ውን የወ​ር​ቁን ዕቃ ሁሉ ሰባ​በረ።


ዓመ​ቱም ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ልኮ ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ደው፤ የከ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ ከእ​ርሱ ጋር አስ​ወ​ሰደ፤ የአ​ባ​ቱን የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ወን​ድም ሴዴ​ቅ​ያ​ስን በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አነ​ገሠ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላ​ቁ​ንና ታና​ሹን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የአ​ለ​ቆ​ቹ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ወሰደ።


ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በ​ረው መቅ​ደስ የወ​ሰ​ደ​ውን፥ ወደ ባቢ​ሎ​ንም መቅ​ደስ ያፈ​ለ​ሰ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የወ​ር​ቁ​ንና የብ​ሩን ዕቃ ንጉሡ ቂሮስ ከባ​ቢ​ሎን መቅ​ደስ አው​ጥቶ ለቤተ መዛ​ግ​ብቱ ሹም ለሲ​ሳ​ብ​ሳር ሰጠ​ውና፦


ለካ​ህ​ና​ትም ለዚ​ህም ሕዝብ እን​ዲህ ብዬ ተና​ገ​ርሁ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሐሰ​ተ​ኛ​ውን ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃ በቅ​ርብ ጊዜ ከባ​ቢ​ሎን ይመ​ለ​ሳል የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ቃል አት​ስሙ።


የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ምን​ቸ​ቶ​ቹን፥ መቅ​ረ​ዞ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹን፥ መን​ቀ​ሎ​ች​ንም፥ የወ​ር​ቁን ዕቃ በወ​ርቅ፥ የብ​ሩ​ንም ዕቃ በብር አድ​ርጎ፥ ወሰደ።