ከአባቱም ሞት በኋላ የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ ያጠፉት ዘንድ መካሪዎች ነበሩትና።
ዕዝራ 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምክራቸውንም ያፈርሱ ዘንድ በፋርሱ ንጉሥ በቂሮስ ዘመን ሁሉ እስከ ፋርስ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ መንግሥት ድረስ መካሪዎችን ገዙባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፋርስ ንጉሥ ከቂሮስ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ እስከ ፋርስ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ድረስ ዕቅዶቻቸውን የሚያሰናክሉ መካሪዎችን በገንዘብ ገዙባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቂሮስ የፋርሱ ንጉሥ ዘመን ሁሉ ጀምሮ እስከ ዳርዮስ የፋርስ ንጉሥ መንግሥት ድረስ ሥራቸውን እንዲያፈርሱ ባለሥልጣኖችን ቀጠሩባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለፋርስ መንግሥት ባለሥልጣኖች ጉቦ በመስጠትም በእነርሱ ላይ ተጽዕኖ ሊያደርጉባቸው ሞከሩ፤ ከቂሮስ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ዳርዮስ እስከ ተነሣበት ዘመን ድረስ ይህን ከማድረግ አልተቈጠቡም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምክራቸውንም ያፈርሱ ዘንድ በፋርሱ ንጉሥ በቂሮስ ዘመን ሁሉ እስከ ፋርስ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ መንግሥት ድረስ መካሪዎችን ገዙባቸው። |
ከአባቱም ሞት በኋላ የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ ያጠፉት ዘንድ መካሪዎች ነበሩትና።
በዚያን ጊዜም በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ ተቋረጠ፤ እስከ ፋርስም ንጉሥ እስከ ዳርዮስ መንግሥት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ተጓጐለ።
በአሕሳዊሮስም መንግሥት፥ በመንግሥቱም በመጀመሪያ ዘመን፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ላይ ደብዳቤ ጻፉ።
የእግዚአብሔር ዐይን ግን በይሁዳ ምርኮኞች ላይ ነበረ፤ ይህም ነገር ወደ ዳርዮስ እስኪደርስ ድረስ፥ መልሱም በመልእክተኛ እስኪመጣ ድረስ አልከለከሉአቸውም።