ንጉሡም ለአዛዡ ለሬሁም፥ ለጸሓፊውም ለሲምሳይ፥ በሰማርያና በወንዝ ማዶም ለተቀመጡትና ለቀሩት ተባባሪዎቻቸው እንዲህ የሚለውን መልስ ላከ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን።
ዕዝራ 4:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሡም የአርተሰስታ መልእክተኛ በደረሰ ጊዜ በአዛዡ በሬሁምና በጸሓፊው በሲምሳይ፥ በተባባሪዎቻቸውም ፊት መልእክቱን ባነበበ ጊዜ ፈጥነው ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አይሁድ በፈረስ ሄዱ፤ በኀይልም አስተዉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሡ የአርጤክስስ ደብዳቤ ቅጅ በሬሁም፣ በጸሓፊው በሲምሳይና በተባባሪዎቻቸው ፊት እንደ ተነበበ፣ ወዲያውኑ በኢየሩሳሌም ወደሚገኙት አይሁድ ሄደው ሥራውን እንዲያቆሙ አስገደዷቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሡም የአርጤክስስ ደብዳቤ ግልባጭ በሬሑምና በጸሐፊው በሺምሻይ በተባባሪዎቻቸውም ፊት በተነበበ ጊዜ ፈጥነው ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አይሁድ ሄዱ፤ በግድና በኃይልም አስተዉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሠ ነገሥቱ አርጤክስስ የላከው የመልስ ደብዳቤም መጥቶ ለረሑም፥ ለሺምሻይና ለተባባሪዎቻቸው ሁሉ እንደ ተነበበላቸው፥ ወዲያውኑ ወደ ኢየሩሳሌም ገሥግሠው በመምጣት ሕዝቡን በማስገደድ የኢየሩሳሌምን ከተማ እንደገና ከመሥራት አገዱአቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንጉሡም የአርጤክስስ ደብዳቤ ግልባጭ በሬሁምና በጸሐፊው በሲምሳይ በተባባሪዎቻቸውም ፊት በተነበበ ጊዜ ፈጥነው ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አይሁድ ሄዱ፤ በግድና በኃይልም አስተዉአቸው። |
ንጉሡም ለአዛዡ ለሬሁም፥ ለጸሓፊውም ለሲምሳይ፥ በሰማርያና በወንዝ ማዶም ለተቀመጡትና ለቀሩት ተባባሪዎቻቸው እንዲህ የሚለውን መልስ ላከ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን።
በዚያን ጊዜም በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ ተቋረጠ፤ እስከ ፋርስም ንጉሥ እስከ ዳርዮስ መንግሥት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ተጓጐለ።
በአርተሰስታ ዘመን በሴሌም፥ ሜትሪዳጡ፥ ጣብሄል፥ የቀሩት ተባባሪውቻቸውም ለፋርስ ንጉሥ ለአርተሰስታ ጻፉ፤ ደብዳቤውም በሶርያ ፊደልና በሶርያ ቋንቋ ተጽፎ ነበር።